የኢክኢሚ አጭር ታሪክ

ዘመኑ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1999 ነበር፡፡ethio.com, ethiolove.com፣ asmarino.com የተባሉ ወዘተ   በተለያዩ አለማዊ የሆኑ ድረ-ገጾችና የውይይት ክፍሎች፡ ውስጥ  Pentew, Christian Man ወዘተ  በተባሉ  በተለያዮ ቅጽል ስሞች በመጠቀም  ነበር በግልጽነት የጌታችንን የየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት እመሰክር የነበረው። 

                
ምስክርነቴንም አዘውትሬ በመቀጠል ላይ ሳለሁ፤ አንዳንድ ሰዎች በግል/Private  በመጻፍ ስለ  ክርስትና ህይወቴና ስለተለያዩ ተመሳሳይ ዕምነትን የተመለከቱ ጉዳዬች ይጠይቁኝና ያነጋግሩኝ ነበር።  ያንን አጋጣሚ ተጠቅመው  እነርሱም ከተለያዩ አገራት፤  ለምሳሌ ከኬንያ፤ ሱዳን፤ ግብጽ ወዘተ ወደ ምዕራቡ ዓለም ከመምጣታቸው በፊት አማኞች ቢሆኑም እንኳን፤  እንደ ቀድሞው በሕይወታቸው እና በቃላቸው ስለ ጌታ የሱስ አዳኝነት ለመመስከር በጣም መቸገራቸውን እና በተለይም ፤ አማኞችን በሚዘልፉና ጸያፍ ቃላት በተሞሉ የውይይት ክፍሎች ውስጥ በአደባባይ በድፍረት እና በግልጽነት እንዴት መመስከር እንደቻልኩኝ የዘወትር ጥያቄዎቻቸው ነበሩ። ለጥያቄዎቻቸው መልስ ሆኖ ያገኘሁትና  ያኔም ሆነ ዛሬም ያለኝ መልስ “ ከእኔ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ ሃይል እና ችሎታውን የሰጠኝ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ያንን አውቃለሁ “ የሚል ነው።