AIM

” እኛ አንድ እንደሆንን እነሱም አንድ ይሆኑ ዘንድ ” ዮሐ 17፤21


ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የክርስቶስ ብርሃን የበራላቸው ሕዝቦች ሁሉ እጅ ለእጅ ተያይዘው ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለተከታዮቹ የሰጠውን ታላቁን ተልዕኮ (ማቴ 28፡19-20) ለመወጣት እንዲችሉ ማገዝና በዚህም ረገድ የእግዚአብሔር መጠቀሚያ ዕቃዎች ለመሆን እንድንችል ያልተቋረጠ የዘወትር ጸሎታችን ነው፡፡ ዳግመኛ የተወለዱና የነፍሳት ድነት ሃሴት የሚሆናቸው በተለያዩ የሃይማኖት ሺንገላዎች ተተብትበው በክርስቶስ ኢየሱስ የሚገኝ የመዳን እውቀት ተሰውሮባቸው የሚገኙትን ሕዝቦቻችንን ለመታደግ (ምሣሌ 24፡11 ) ጌታ በልባቸው ሸክም ያስቀመጠ ቅዱሳን ሁሉ ይህን ክፍል በመጠቀም የታላቁ ተልዕኮ መሳካት ተባባሪዎች እንዲሆኑ ማገዝና ማበረታተት ዋነኛ ዓላማችን ነው፡፡በተጨማሪም

1.በሳይበር ዓለም (ኢንተርኔት) የመዳንን ወንጌል ለመስበክ፡፡ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀመዛሙርቴ አድርጓቸው፡፡(ማቴ 28፡20)

2.ወንጌልን በመስበክ በተለያዩ በዲያብሎስ ወጥመድ ስር የወደቁትን ነጻ ለማውጣትና በክርስትና ሕይወት የደከሙትን እንደገና ወደ ጌታ እንዲመለሱ ለመርዳት 1ኛ ዮሐ 1፡8

3.የወንጌል ስብከት በማይፈቀድባቸው አካካባቢዎች የሚኖሩትን በኢንተርኔት ለመድረስና ሕብረትና መጽናናት እንዲያገኙ ለማገዝ

4.በመኖሪያ ቤታቸውና በስራ ቦታቸው እንዲሁም በትምሕርት ቦታቸው የኢንተርኔት ግንኙነት ያላቸው ከሌሎች ጋር በመቀራረብ ያልተቋረጠ ኀብረት እንዲኖራቸው የተከፈተ በር ለመሆን

5.የክርስቲያን መረጃ ልውውጥን ለማቀላጠፍና በተላያዩ አገሮች በተበተኑ ክርስቲያኖች ሕይወት እግዚአብሔር እየሰራ ያለውን ድንቅ ስራ ለማሳወቅና በእምነታቸው ምክንያት ችግርና ስቃይ እየደረሰባቸው ያሉትን በጸሎት ማገዝ

6.በእምነት የበረቱ የጌታ ጸጋ የበዛላቸው ወገኖች ሌሎችን እንዲያበረቱና እንዲያነቃቁ አመቺ መድረክ መክፈት

7.እያንዳንዱን አማኝ በማበረታታት በማገዝና በማደፋፈር በየአጠቢያ ቤተክርስቲያኑ ጠንካራ ክርስቲያን እንዲሆንና ቤተክርስቲያኑን በሁሉም መስክ የሚያግዝ እንዲሆን ለማበረታታት፡፡

8.ለአፍሪካ ቀንድ በተለይም ለኢትዮጵያና ለኤርትራ በመጸለይና ስብከተ ወንጌል ያለምንም ተጽዕኖ እንዲሰበክና የክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅነት የሚቃወም ሰይጣናዊ እምነት አቅም እንዲያጣ መጸለይ

9.ወደዚህ ክፍል የሚመጡ ክርስቲያኖች በተለያዩ ክፍለ እምነቶች (denominations) መከፋፈልን መለያየትንና መካሰስን አስወግደው በአንድ ልብ ለአንድ የክርስቶስ መንግስት ስራ እንዲሰለፉ ማሳወቅ

10.ከቋንቋ ከነገድ ከዘር ከብሔር ያለፈ አንድ ክርስቲያናዊ ወንድማማችነት ለማስፈን

11.የእግዚአብሔርን ቃል ለመስበክ ለመመስከር ለማስተማርና ለማጽናናት ለሚፈልጉ ክርስቲያኖች የአገልግሎት በር መክፈት