ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ

introdu

ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ

ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ (ኦሪትዘጸአት 8፡1) የሚለው ቃል በባርነት ተይዞ የነበረውን የእስራኤል ሕዝብ ከፈርዖን ለማስለቀቅ የተሰጠ አምላካዊ ትዕዛዝ ነው፡፡
ዛሬም በመንፈሳዊ ዕስራት ውስጥ ተተብትቦ ያለው ሕዝብ የባርነት ሃሳብና እስራት ውስጥ ሆኖ ለአዲሱ መንፈሳዊስርዓት ግንባታ ምንም አስተዋጽዖ ሊያበረክት አይችልም፡፡የግብጽ አስተሳሰብ የባርነት አስተሳሰብ ነው፡፡በግብጽ በባርነትውስጥ የነበሩ እስራኤላውያን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ቀኑን የት እንደሚውሉ ምን እንደሚሰሩ ዕቅድ የማውጣት መብትአልነበራቸውም፡፡
እስራኤላውን በስደት ዘመናቸው ጌቶቻቸው ግብጻውያን በወሰኑት ውሳኔ ውስጥ፣ ያለ ምንም ምርጫ፣ ባልፈለጉትናባላመኑበት ቦታ፣ ሕይወታቸውንና ጉልበታቸውን የሚያውሉ ነበሩ፡፡
ክርስቲያኞች ይህን ከመሰለ የዓለም ባርነት “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነትእንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤” 1ኛ ጴጥሮስ 2፡9ተብሎ እንደተጻፈ የተጠራንበት ዓላማና ግብ ደግሞ፣ የእርሱን በጎነት ለመናገር፣ለንጉሥ ካህናትና፥ ለቅዱስ ሕዝብነት ፥እንዲሁም ለርስቱ የተለየ ወገን ልንሆን መሆኑን አውቀን ነጻ ለመሆን እንደተለቀቀ ሕዝብ ኖረን ለማረፍ ሕይወታችንንእናስተካክል ዘንድ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ልንወስን ይገባል፡፡